Fana: At a Speed of Life!

በ24 ሰዓታት ውስጥ 872 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7 ሺህ 726 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 872 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ በእለታዊ መግለጫው በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 77 ሺህ 860 መድረሱን አመልክቷል።
በሌላ በኩል 648 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 32 ሺህ 325 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በ24 ሰዓታቱ ውስጥ የሰባት ሰዎች ህይወት አልፏል።
በአሁኑ ወቅት 278 ሰዎች በበሽታው በፅኑ ታመዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.