Fana: At a Speed of Life!

በ24 ሰዓታት 1ሺህ 38 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ13 ሰዎች ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 17 ሺህ 323 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሺህ 38 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ይህን ተከትሎም በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 27 ሺህ 242 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።

ከዚህ ባለፈ የ13 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 492 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 232 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 660 መድረሱም ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.