Fana: At a Speed of Life!

በ24 ሰዓታት 540 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 4 ሺህ 493 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 817 የላብራቶሪ ምርመራ 540 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ባለፉት 24 ሰዓታት የ6 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 706 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 4 ሺህ 493 ሰዎች ከኮሮና ቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 73 ሺህ 808 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 636 ሺህ 729 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 110 ሺህ 074 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 34 ሺህ 558 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 323 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.