Fana: At a Speed of Life!

በ24 ሰዓታት 769 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ14 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 5 ሺህ 271 የላብራቶሪ ምርመራ 769 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ባለፉት 24 ሰዓታት የ14 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 681 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 505 ሰዎች ከኮሮና ቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 67 ሺህ 506 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን ለ1 ሚሊየን 621 ሺህ 40 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 108 ሺህ 438 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 39 ሺህ 244 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 309 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.