Fana: At a Speed of Life!

በ300 ወረዳዎች የ10 ዋና ዋና ሰብሎች ልማት በኩታ ገጠም እየተከናወነ ነው-የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ 300 ወረዳዎች አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ የ10 ዋና ዋና ሰብሎች ልማት በኩታ ገጠም እየተከናወነ መሆኑን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ገለጸ።
ኤጀንሲው በሙከራ ደረጃ የተጀመረው የኩታ ገጠም ሰብል ልማት ያለበትን ሁኔታ የዳሰሰ የምክክር መድረክ በአዳማ እያካሄደ ይገኛል።
በኤጀንሲው የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ሲኒየር ዳይሬክተር ዶክተር ዳኛቸው ሉሌ ÷የግብርና ምርቶችን የውጭ ተፈላጊነት ለማሳደግ የግብርና ልማቱ ገበያ ተኮር መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።
በኩታ ገጠም በማልማት የምርት ጥራትና ብዛትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ ስንዴ፣ ጤፍ፣ የቢራ ገብስ፣ በቆሎ እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬን በኩታ ገጠም ማልማት መጀመሩን ጠቅሰዋል።
ከአትክልትና ፍራፍሬ ውስጥ ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ሙዝ፣ አቮካዶና ፓፓያ በኩታ ገጠም እየለሙ ይገኛሉም ነው ያሉት።
300 ወረዳዎች ውስጥ የኩታ ገጠም ሰብል ልማት መጀመሩን ጠቅሰው፤ በኩታገጠም የእርሻ ልማት 1 ነጥብ 9 ሚሊየን አርሶ አደሮች ተሳታፊ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በዚህም÷ በዋና ዋና ሰብሎች ምርትና ምርታማነት ዕድገት ላይ ተስፋ ሰጪ ጅምር ውጤቶች መኖራቸውን አመልክተዋል።
በኤጀንሲው የግብይትና አግሮ ቢዝነስ ዳይሬክተር አቶ ሄኖክ መስፍን በበኩላቸው ÷በአሁኑ ወቅት የአርሶ አደሩን የገበያና የምርት ማከማቻ ችግር ለመቅረፍ የምርት ማሰባሰቢያ ማዕከላት በኦሮሚያና አማራ ክልል ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.