Fana: At a Speed of Life!

በ4 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የተገነባው የስነ አዕምሮ ህክምና መስጫ ህንፃ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አማኑኤል የአዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ4 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ወጪ ያስገነባውን የስነ አዕምሮ፣ ድንገተኛ ህክምና እና የእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎት መስጫ ህንፃን አስመረቀ።

ህንጻው የተገነባው ሙሉ በሙሉ ሃይኒከን አፍሪካ ፋውንዴሽን ባደረገው ድጋፍ ነው።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የሃይኒከን አፍሪካ ፋውንዴሽን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኢዳኦ ፈጆ፣ የማህበረሰብ ተወካዮች እና የሆስፒታሉ ሰራተኞች ተገኝተዋል።

የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኢዳኦ ፈጆ በጊዜ ሂደት የህክምና ሁኔታው እየተሻሻለ እና የባለሙያ እጥረት እየተቀረፈ ቢመጣም የመሰረተ ልማት ችግር ግን አሁንም አስቸጋሪ ሆኖ መቀጠሉን አንስተዋል።

ሆስፒታሉ በቀን በተመላላሽ ህክምና ብቻ ለ580 ያህል የአዕምሮ ህሙማን አገልግሎት እየሰጠ መቆየቱንም ጠቅሰዋል።

ህንጻው ለተለያዩ የስነ አዕምሮ ድንገተኛ ህክምና እና ለእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎት መስጫ የሚውሉ 23 ክፍሎች እንዳሉት ከሆስፒታሉ የፌስ ቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.