Fana: At a Speed of Life!

በ53 ሚሊየን ብር ወጪ የስድስት የመስኖ ጥናትና ዲዛይን ክለሳ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ2014 በጀት ዓመት ጀምሮ ወደ ግንባታ የሚገቡ የስድስት የመስኖ ጥናትና ዲዛይን ክለሳ  በ53 ሚሊየን ብር ወጪ እየተከናወነ እንደሚገኝ የመስኖ ልማት ኮሚሽን አስታወቀ

በሶስት ክልሎች በመከናወን ላይ ያሉት የስድስት የመስኖ ጥናትና ዲዛይን ክለሳ ፕሮጀክቶች በ2013 በጀት ዓመት ቀሪ ወራት  ሙሉ ለሙሉ  ይጠናቀቃሉ ተብሏል፡፡

የመስኖ ጥናትና ዲዛይን ክለሳ ፕሮጀክቶቹ  የሚከናወኑት በአማራ ክልል ሶስት፣ በኦሮሚያ ክልል ሁለት  እና  በደቡብ  ክልል አንድ   መሆናቸው ተጠቁሟል።

የመስኖ ፕሮጀክት የመገጭ መስኖ  መሰረተ ልማት፣  የግልገል አባይ  ግድብና መስኖ መሰረተ ልማት፣ የጀማ ግድብና መስኖ መሰረተ ልማት ፣ የገላና ግድብና መስኖ መሰረተ ልማት  ፣የጎሎልቻ ግድብና መስኖ መሰረተ ልማት እና የብላቴ ግድብና መስኖ መሰረተ ልማት   ናቸው፡፡

የጥናትና ዲዛይን  ክለሳ ስራውን  እየሰሩ ያሉት የአምስቱን ፕሮጀክቶች የየክልሎቹ  የጥናትና ዲዛይን ኢንተርፕራይዞች /ኮርፖሬሽኖች  ሲሆኑ  የብላቴ ግድብና መስኖ መሰረተ ልማትን  ደግሞ የኢትዮጵያ  ኮንስትራክሽን  ዲዛይንና  ሱፐርቭዥን ስራዎች ኮርፖሬሽን ነው፡፡

የፕሮጀክቶቹ የጥናትና ክለሳው ስራ ተጠናቆ ወደ ግንባታ ሲገቡ 64 ሺህ 253 ሄክታር  የማልማት አቅም እንደሚኖራቸው ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.