Fana: At a Speed of Life!

በ782 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ከሕወሓት ቡድን ጋር በመቀናጀት ግጭቶች ሲያስነሱ፣ ግድያ እና ዝርፊያ ሲፈጽሙ የነበሩ 782 የኦነግ ሸኔ የጥፋት ኃይሎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ክልል መንግስት አስታወቀ፡፡

የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት መንግስት የክልሉን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል፡፡

ሰሞኑን በሆሮ ጉዱሩ ወለጋና በሌሎች ዞኖች ብሄርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች እንዲቀሰቀስ በማድረግ ግድያ በፈጸሙ የህወሓት ጁንታ ተላላኪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱንም ገልጸዋል፡፡

ከወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ ህግን ማስከበር ባቃታቸውና ከኦነግ ሼኔ ቡድን ጋር በመሆን በንጹሃን ዜጎች ላይ የጥፋት ተግባር ሲፈጽሙ በነበሩ የመንግስት አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱንም አስታውቀዋል፡፡

ይህም የክልሉ መንግስት ሰላምና መረጋጋትን ማረጋገጥ አልቻለም በሚል በተለያዩ ወገኖች ለሚቀርበው ወቀሳ መልስ ሊሆን ይችላልም ነው ያሉት፡፡

ህግ ለማስከበር በተሰራው ስራ ከከባድ እስከ ቀላል የጦር መሳሪያዎች መያዛቸውንም ነው ያስታወቁት፡፡

ከዚህ በኋላም ኦሮሚያ ክልል ውስጥ ብሄርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶችን ለመቀስቀስ የሚንቀሳቀሱ የጥፋት ሃይሎችን የክልሉ መንግስት እንደማይታገስም አስረድተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.