Fana: At a Speed of Life!

ቡበከር ናስር ለሙከራ ጊዜ ወደ ደቡብ አፍሪካ ማቅናቱ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ጥር 17፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች እና የምንጊዜውም ኮከብ ግብ አግቢ አቡበከር ናስር ለሙከራ ጊዜ ወደ ደቡብ አፍሪካ አቅንቷል።

አቡበከር ናስር ወደደቡብ አፍሪካ ያቀናው፥ የአገሪቱ ክለብ ማሜሎዲ ሰንዳውስ በጥር የዝውውር መስኮት ተጫዋቹን ለማስፈረም ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የዝውውር ድርድር ካደረገ በኋላ ነው፡፡

የደቡብ አፍሪካው ክለብ አቡበከርን ለሙከራ መጥራቱን ተከትሎ ትላንት ማምሻውን ወደ ደቡብ አፍሪካ መጓዙ ነው የተገለፀዉ።

በሙከራው ጊዜ የትራንስፖርት እና ደቡብ አፍሪካ በሚቆይበትም ጊዜ ሙሉ ወጪውን ክለቡ የሚችል መሆኑን የኢትዮጵያ ቡና ክለብ አሳውቋል።

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.