Fana: At a Speed of Life!

ቡና ባንክ ለመምህራንና ለጤና ባለሙያዎች አዲስ የቁጠባ አገልግሎት ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቡና ባንክ ለመምህራን እና ለጤና ባለሙያዎች አዲስ የቁጠባ ሽልማት መርሃ ግብር በይፋ መጀመሩን አስታወቀ።

ባንኩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ÷ በሁሉም ደረጃ ላይ የሚገኙ መምህራን እና የጤና ባለሙያዎች ተካፋይ በሚሆኑበት በዚህ አዲስ የቁጠባ መርሃ ግብር ላይ ለሚሳተፉ ደንበኞቹ  ባንኩ የተለያዩ ሽልማቶችን ማዘጋቱን ገልጿል።

በዚህ የቁጠባ አገልግሎት ላይ ለመሳተፍ ማናቸውም በመምህርነት ሙያ ላይ የተሰማሩና ከመዋዕለ ህጻናት ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ድረስ የሚያገለግሉ መምህራን ፣ እንዲሁም በትምህርት አስተዳደርና ድጋፍ ስራዎች ላይ የሚገኙ ሁሉ ብቁ መሆናቸውንም አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይም በጤናው ዘርፍ የተሰማሩ ነርሶች፣ የጤና መኮንኖችና ጤና ረዳቶች፣ የማህበረሰብ ጤና ባለሙያዎች፣ የህክምና ዶክተሮች፣ ራዲዮሎጂስቶች እንዲሁም ከህክምና ሙያ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ስራዎችን የሚያከናውኑ እና በህክምና ተቋማት ውስጥ በድጋፍ ሰጪነት የሚያገለግሉ ባለሙያዎች ሁሉ የዚህ የቁጠባና ሽልማት መርሃ ግብር ተሳታፊ ለመሆን ብቁ ናቸው ብሏል።

በቁጠባ አገልግሎቱ ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ቁጠባውን እንደጀመሩ ተሸላሚ የሚያደርጋቸውን የዕጣ ቁጥር የሚቀበሉ ሲሆን ከ400 ብር ጀምሮ መቆጠብ ለሽልማቱ ብቁ ያደርጋል።

የባለሙያዎቹ የቁጠባ መጠን ባደገ ቁጥርም ዕድለኛ የሚያደርጋቸው ዕጣ ቁጥሮች መጠን በዚያው ልክ የሚያድግ ይሆናል ነው ያለው ባንኩ።

ባንኩ በቀጣይ የሚያካሂደው ይኸው ይቆጥቡ ይሸለሙ ፕሮግራም ሲጠናቀቅ ያዘጋጃቸውን ሽልማቶች በብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ድርጅት ውስጥ በይፋዊ ስነስርዓት ዕጣ በማውጣት አሸናፊዎቹን ያሳውቃልም ነው ያለው።

በዚህ መሰረት ለሽልማት የተዘጋጁት አንድ ዘመናዊ 2020 ሞዴል ሱዙኪ ዲዛየር መኪና ፣ 12 ዘመናዊ ላፕቶፖችና 12 ታብሌቶች እንዲሁም 24 ስማርት የሞባይል ስልክ ቀፎዎች፣ ስድስት የእረፍት ጊዜ ሽርሽር ሙሉ ወጪ የተሸፈነላቸው የታሪካዊ ቦታዎች ጉብኝትፓኬጆች ለአሸናፊዎቹ እንደሚተላለፉም ነው የተገለጸው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.