Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ ለሁለት የቴሌኮሙዩኒኬሽን ፈቃዶች 12 የፍላጎት ጥያቄ መቀበሉን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን ለሁለት የቴሌኮሙዩኒኬሽን ፈቃዶች ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ተቋማት የፍላጎት ጥያቄ መቀበሉን አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣኑ ከቴሌኮም ፈቃዶች ጋር በተያያዘ የፍላጎት መግለጫውን ከአንድ ወር በፊት ይፋ ማድረጉን አስታውሷል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ፍላጎታቸውን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያስገቡ ቀነ ገደብ አስቀምጦም ነበር፡፡

በዚህ ሂደትም በቀነ ገደቡ ማብቂያ ለቴሌኮሙዪኒኬሽን ፈቃዶቹ 12 የፍላጎት ጥያቄ እንደቀረበለትም ነው ያስታወቀው፡፡

ከእነዚህ ውስጥ 9ኙ በቴሌኮም ዘርፍ የሚሰሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ ከቴሌኮም ዘርፍ ውጭ የሚሰሩ ናቸው ብሏል፡፡

ከእነዚህ መካከል ቮዳኮም፣ ሳፋሪኮም፣ ኢቲሳላት፣ አዢያን፣ ኤም ቲ ኤን፣ ኦሬንጅ፣ የሳዑዲ ቴሌኮም ኩባንያን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ዓለም አቀፍ ተቋማት እንደሚገኙበትም ገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.