Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት በሚፈጥሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት በሚፈጥሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ÷በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የኢኮኖሚ አሻጥር ለመፍጠር ሲባል ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት መፈጠሩ መረጋገጡን አንስቷል፡፡

ለአብነትም በተለያዩ ከተሞች እና ጫካዎች ጭምር ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች መገኘታቸው ነው በመግለጫው የተመላከተው፡፡

ባለስልጣኑ መሰል ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት በሚፈጥሩ አካላት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድም አስጠንቅቋል፡፡

በዚህ መሰረት ነዳጅን ሆን ብለው በተለያየ መንገድ የደበቁም ሆነ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ነዳጅ አቅራቢዎችም ሆኑ ማደያዎች እስከ ዛሬ 10 ሰዓት ድረስ አቅርቦቱን ካላሻሻሉ እና ወደ ትክክለኛው መስመር ካልገቡ ከእገዳ እስከ መውረስ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጿል፡፡

በተስፋዬ ከበደ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.