Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ 361 ኪ.ሜ የተበላሸ መንገድ ጠግኖ ለአገልግሎት ክፍት አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን 361 ኪ.ሜ የተበላሸ መንገድ እና የመንገድ አካላትን ጠግኖ ለአገልግሎት ክፍት አደረገ።
በዚህም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተበላሹ የአስፋልት፣ የጠጠር ፣ የእግረኛ መንገድ፣ የመንገድ ዳር መብራት፣ የድልድይ ጥገና እንዲሁም የፍሳሽ ማስወገጃ ፅዳት አከናውኗል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በስድስት ወራት 350 ኪሎ ሜትር ልዩ ልዩ መንገድ ለመጠገን አቅዶ 361 ኪሎ ሜትር ማከናወኑ ተገልጿል።
ባለስልጣኑ የመንገዶችን የብልሽት ደረጃ በጥናት በመለየት ሲሆን የጥገና ስራውም የትራፊክ እንቅስቃሴን እንዳያስተጓጉል በእረፍት ቀናት እና በሌሊት ክፍለ ጊዜ ጭምር እያከናወነ እንደሚገኝም ነው የተገለጸው።
የአስፋልት መንገዶች ጥገና ስራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካልም ከጦርሃይሎች – አየር ጤና፣ ከሆላንድ ኤምባሲ – ቀራንዮ፣ ከአስኮ መናሃሪያ – ዊንጌት አደባባይ፣ ከቴዎድሮስ አደባባይ – ቤተ መንግስት፣ ከአራት ኪሎ – ፒያሳ፣ ከቸርችል -ፒያሳ፣ ከሸራተን መጋጠሚያ – ፓርላማ፣ ከሳሪስ አዲስ ሰፈር፣ ጀሞ 1፣2፣ 3 ኮንዶሚኒየም፣ ከለቡ መጋጠሚያ – ጀርመን፣ ከጎፋ ገብርኤል – ጀርመን፣ ከአፍንጮ በር – ሰሜን ሆቴል፣ ከፓስተር ወረዳ 8 አካባቢ – እንቁላል ፋብሪካ፣ ከእግዚአብሔር አብ – ሜታ አቦ የሚጠቀሱ ናቸው ተብሏል፡፡
ከዚያም ባለፈ ፓስተር ወረዳ 8 አካባቢ፣ ከካራ ቆሬ -ጀሞ፣ ቦሌ ለሚ፣ ጎሮ፣ ሰሚት ኮንዶሚኒየም፣ አያት አዲስ መንደር ያሉ የጠጠር መንገዶችም ጥገና ከተደረገላቸው መካከል የተወሰኑት መሆናቸው ተመላክቷል።
የድሬኔጅ መስመር ፉካና ቦይ ጠረጋ እና የድሬኔጅ መስመሮች እድሳት ጥገና ከተደረገላቸው መካከልም፡- ከሃና – ማሰልጠኛ፣ ከጀሞ 1 – ጀሞ 3፣ ገላን ኮንዶሚኒየም፣ ሃይሌ ጋርመንት አካባቢ፣ ከሳሪስ አደይ አበባ – ካዲስኮ፣ ከጦርሃይሎች – ቶታል፣ ገርጂ ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ፣ ሲ.ኤም.ሲ አካባቢ፣ ቦሌ ሚካኤል – ቦሌ ብራስ፣ አያት አዲስ መንደር፣ ኢምፔሪያል – አንበሳ ጋራጅ አካባቢ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
በቀጣይም ባለስልጣኑ መንገዶች ከመበላሸታቸው በፊት ቀድሞ በመጠገን የመንገዶችን የአገልግሎት እድሜ ለማራዘም እና የእግረኞችን እና ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ምቹ ለማድረግ እንደሚሰራ ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.