Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት አራት ወራት ውስጥ በወርቅ ምርት የተሻለ ገቢ ማግኘት ተችሏል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት አራት ወራት የወርቅ ምርትን ወደ ውጪ ሃገር በመላክ የተሻለ ገቢ ማስገባት መቻሉን የማዕድን እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስታወቁ፡፡
በአራት ወራት ውስጥ ከወርቅ ምርት በተጨማሪ ቡና፣ አበባ እና ጫት ከፍተኛ የወጪ ንግድ ድርሻ ያላቸው ዘርፎች መሆናቸውም ታውቋል፡፡
በአራት ወራት ውስጥ ወርቅ 265 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር፣ ቡና 230 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር፣ አበባ 138 ነጥብ 3 ሚሊየን ዶላር እንዲሁም ጫት 129 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ገቢ በማስገባት ከፍተኛውን ድርሻ ይዘዋል ተብሏል፡፡
በቀጣይ ወራትም ግዙፍ ኩባንያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ወደ ማዕድን ምርት እየገቡ በመሆኑ የተሻለ ስራ በመስራት የተሻለ ውጤት የሚመዘገብበት ይሆናል ሲሉም አስታውቀዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.