Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የ26 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 583 ደግሞ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የ26 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 583 ደግሞ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ሚኒስትሯ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ እንዳሰፈሩት በ24 ሰዓታት 6 ሺህ 907 የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸው 583 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

በዚህም በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 19 ሺህ 289 ደርሷል።

እንዲሁም በቫይረሱ ምክንያት ባለፉት 24 ሰዓታት የ26 ሰዎች ሲያልፍ በዚህ በሀገሪቱ በቫይሩ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 336 መድረሱን ነው ሚኒስትሯ ያስታወቁት።

በአሁን ወቀት በሀገሪቱ 145 ፅኑ ህሙማን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝም ተነግሯል።

በሌላ በኩል በ24 ሰዓታት ወስጥ 330 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.