Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት ተጨማሪ 2 ሺህ 316 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 2 ሺህ 316 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደገለጹት÷ለ 8ሺህ 247 ዜጎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ነው 2 ሺህ 316 ዜጎች ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠው፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት 11 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት መዳረጋቸውንም ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
በሌላ በኩል 51 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን÷375 ዜጎች ደግሞ በጽኑ ህክምና ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ ነው የገለጹት፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.