Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 789 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 12 ሺህ 164 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራዎች 789 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ይህንንም ተከትሎ በሀገሪቱ በአጠቃላይ እስካሁን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 63 ሺህ 367 ደርሷል።

በሌላ በኩል 384 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 24 ሺህ 024 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በ24 ሰዓታት ውስጥ የ12 ሰዎች ህይወትም በቫይረሱ ምክንያት አልፏል።

347 ሰዎችም በአሁኑ ወቅት በፅኑ መታመማቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመልከታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.