Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 365 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 783 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 473 የላቦራቶሪ ምርመራ 365 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ዶክተር ሊያ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት 783 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ ምክንያት 5 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

እስካሁን በወረርሽኙ ምክንያት 2 ሺህ 71 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው 11 ሺህ 860 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 231 ሰዎች ደግሞ በጽኑ የታመሙ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡

ወረርሽኙ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ ለ1 ሚሊየን 924 ሺህ 136 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል፡፡

ከእነዚህም መካከልም 134 ሺህ 132 በወረርሽኙ የተያዙ ሲሆን አሁን ላይ 11 ሺህ 860 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.