Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 451 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 1 ሺህ 24 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 4 ሺህ 639 የላቦራቶሪ ምርመራ 451 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ዶክተር ሊያ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት 1 ሺህ 24 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ ምክንያት 8 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

እስካሁን ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች 109 ሺህ 293 ሲደርስ 1 ሺህ 909 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው 11 ሺህ 660 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 224 ሰዎች ደግሞ በጽኑ የታመሙ መሆናቸውን ነው የገለጹት፡፡

ወረርሽኙ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ ለ1 ሚሊየን 780 ሺህ 961 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል፡፡

ከእነዚህም መካከልም 122 ሺህ 864 በወረርሽኙ የተያዙ ሲሆን አሁን ላይ 11 ሺህ 660 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.