Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 552 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ9 ሺህ 203 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 552 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሯ አሁን ላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 21 ሺህ 452 መድረሱን በፌስ ቡክ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ባለፉት 24 ሰአታት 388 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ 9 ሺህ 415 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የ15 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ 380 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በተጨማሪም 174 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ ይገኛሉም ነው ያሉት፡፡

በኢትዮጵያ እስካሁን ለ478 ሺህ 17 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 21 ሺህ 452 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

አሁን ላይ 11 ሺህ 655 ሰዎች በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ይገኝባቸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.