Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 640 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ 14 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5 ሺህ 284 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 640 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
 
በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 74 ሺህ 584 ደርሷል።
በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የ 14 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
 
በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎቸ ቁጥር 1 ሺህ 191 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት መረጃ ያመለክታል።
 
በ24 ሰዓታት ውስጥ 199 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 30 ሺህ 952 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
 
እንዲሁም 271 ሰዎች ፅኑ ህሙማን ማዕከል ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸውይገኛል ተብሏል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.