Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 730 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 7 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 475 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 730 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 76 ሺህ 98 ደርሷል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የ 7 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎቸ ቁጥር 1 ሺህ 205 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት መረጃ ያመለክታል።

በ24 ሰዓታት ውስጥ 226 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 31 ሺህ 430 ደርሷል።

እንዲሁም 255 ፅኑ ህሙማን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ተብሏል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.