Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 976 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን የ15 ሰዎች ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 19 ሺህ 449 የላብራቶሪ ምርመራ 976 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 59 ሺህ 648 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው እለታዊ መረጃ ያመለክታል።

በ24 ሰዓታት ውስጥ የ15 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 933 ደርሷል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው ዕለት 482 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 21 ሺህ 789 መድረሱ ነው የተገለጸው።

እስካሁን በኢትዮጵያ ለ1 ሚሊየን 63 ሺህ 454 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 59 ሺህ 648 ሆኗል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 36 ሺህ 924 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 309 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.