Fana: At a Speed of Life!

ባምላክ ተሰማ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታን ይመራል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው የመሃል ዳኛ ባምላክ ተሰማ የአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግን ይመራል።

ኢትዮጵያዊው የመሐል ዳኛ ቲፒ ማዜምቤ በሜዳው ከሞሮኮው ራጃ ካዛብላንካ ጋር የሚያደርጉትን የቻምፒየንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ የሚመራ ይሆናል።

የመጀመሪያው ጨዋታ በመጭው አርብ ካዛብላንካ ላይ የሚደረግ ሲሆን የመልሱ ጨዋታ ደግሞ ሉሙምባሺ ላይ መጋቢት ወር ላይ የሚደረግ ይሆናል።

ከወራት በፊት የግብፁ ዛማሊክና የዛምቢያው ዜስኮን ጨዋታ ከረዳቶቹ ተመስገን ሳሙኤልና ለሚ ንጉሴ ጋር በመሆን መምራቱን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.