Fana: At a Speed of Life!

ባየር ሙኒክ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ለ6ኛ ጊዜ አነሳ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጀርመኑ ባየር ሙኒክ የፈረንሳዩን ፓሪስ ሴንት ጀርመንን በመርታት ቻምፒየንስ ሊጉን ለ6ኛ ጊዜ አንስቷል።

የ2019/2020 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ትናንት ምሽት በፖርቹጋል ዋና ከተማ ሊዝበን ተካሂዷል።

በፍፃሜው የጀርመኑ ባየር ሙኒክ ከፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ጀርመን የተገናኙ ሲሆን፦ ባየር ሙኒክ ጨዋታውን 1 ለ 0 አሸንፏል።

የባየር ሙኒክን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎልም ኪንግስሌይ ኮማን በ59ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል።

ይህን ተከትሎም የጀርመኑ ክለብ የ2019/2020 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል፤ ሙኒክ የትናንት ምሽቱን ጨምሮ ዋንጫውን ለ6ኛ ጊዜ ማንሳት ችሏል።

ባየር ሙኒክ የቻምፒየንስ ሊጉን ዋንጫ ከሪያል ማድሪድ (13) እንዲሁም ኤሲ ሚላን (7) ቀጥሎ ከእንግሊዙ ሊቨርፑል ጋር እኩል 6  ጊዜ አሳክቷል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.