Fana: At a Speed of Life!

ባይደን በማይናማር የመፈንቅለ መንግስት የጦር አመራሮች ላይ ማዕቀብ ጣሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በማይናማር የመፈንቅለ መንግስት የጦር አመራሮች ላይ ማዕቀብ ጣሉ፡፡

ባይደን ስልጣን ከያዙ ወዲህ ማዕቀብ ሲጥሉ ይህ የመጀመሪያቸው ነው፡፡

የማይናማር አመራሮች በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡትን አሳን ሱ ኪን ወደ ስልጣን እንዲመልሱ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ማዕቀቡ ከጦር አመራሮቹ በተጨማሪ ቤተሰቦቻቸውንና ከጦሩ ጋር የንግድ ግንኙነት ያላቸውንም ያካተተ ነው ተብሏል፡፡

ባይደን ሰሞኑን የማይናማር ጦርን በመቃወም ለተቃውሞ አደባባይ የወጣውን ህዝብ በማስመልከትም ዓለም ትግላቸውን እየተመለከተ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አንዳንዶቹ የጦር አመራሮች ከዚህ ቀደም በሮሂንጊያ ሙስሊሞች ላይ ባደረሱት በደል አማካኝነት ማዕቀብ የተጣለባቸው ናቸው ተብሏል፡፡

ተቃውሞ የበረታበት የመፈንቅለ መንግስቱ አመራር በበኩሉ አሁንም ሰዎችን እያሰረ ሲሆን የተለያዩ ክለከላዎችንም አውጇል፡፡

ከዚህ በተቃራኒው ጦሩ በሀገሪቱ ህዳር ላይ የተካሄደው ምርጫ “ተጭበርብሯል” ብለው በሚያምኑ የሀገሪቱ ተቃዋሚዎች ድጋፍ እንደተቸረውም ተሰምቷል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.