Fana: At a Speed of Life!

ብልጽግና ብቁ መሪዎችን ለማፍራት እንደሚተጋ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የብልጽግና ጉዞው ለኢትዮጵያ ትርጉም ያለው ለውጥ ከማሳካት በዘለለ ብቁ መሪዎችን ለማፍራት እንደሚተጋ አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ እንደ ንስር የሩቁን የሚመለከቱ፤ ከዋናው ዓላማቸው ሳይዛነፉ ግባቸውን የሚመቱ፤ በትጋት አሻራቸውን አኑረው የሚያልፉ ጽኑ መሪዎች ብሩህ ነገን ይተልማሉ ብለዋል፡፡

አያይዘውም ከነጠላ ጉዳይ ይልቅ ምሉዕ እይታን የሚያስቀድሙና ከችግር በላይ ከፍ ብለው መፍትሄ የሚያፈልቁ ዜጎች ውድ የሀገር ሀብቶች መሆናውንም ጠቁመዋል፡፡

እንቅፋትና ጋሬጣውን አልፈው፣ መውደቅና መነሳቱን ተቋቁመው ድል የሚያስመዝግቡ ብርቱ ወጣቶች የኢትዮጵያ የመጭው ዘመኗ መሀንዲሶች መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያም እነሱን ይዛ የማይቀለበስ የስኬት ጫፍ ትደርሳለችም ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.