Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለትግራይ መልሶ ማቋቋም የሚውል የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለትግራይ ክልል መልሶ ማቋቋም ስራ የሚውል የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ ክልሉን መልሶ ለመገንባት ሁሉም እንዲረባረብ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የተደረገ መሆኑም ተገልጿል።

በትግራይ ክልል የተካሄደውን የሕግ ማስከበር ስራ በከፍተኛ ሁኔታ ሲያግዝ የቆየው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አሁንም የክልሉ ህዝብ ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ ኑሮው እስከሚመለስ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ድጋፉ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አለመሆኑን ጠቅሰው፥ ተቋሙ ወደፊትም የክልሉን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን እንቅስቃሴ መደገፉን እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

አሁን ወቅቱ የትግራይ ህዝብ ከሁሉም ወገኖቹ ወንድማዊ ፍቅርና ድጋፍ የሚፈልግበት ነው ያሉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ በበኩላቸው ድጋፉ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ለትግራይ ህዝብ ያለውን አጋርነት ያሳየበት መሆኑን ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.