Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ ቡድኑ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ለሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የቀን ለውጥ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ወንዶች ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ለሚያደርጋቸው ጨዋታዎች የቀን ለውጥ መደረጉን ካፍ አስታውቋል፡፡፡

በአይቮሪ ኮስት አዘጋጅነት በፈረንጆች 2023 በሚደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳታፊ ለመሆን የሚደረጉ ጨዋታዎች ከቀናት በኋላ መካሄድ የሚጀምሩ ሲሆን፥ “በምድብ መ” ከግብጽ፣ ጊኒ እና ማላዊ ጋር የተደለደለችው ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎቿን ከማላዊ እና ግብጽ ብሄራዊ ቡድኖች ጋር ታከናውናለች፡፡

ጨዋታዎቹ ግንቦት 25 እና 29 እንዲደረጉ አስቀድሞ መረሐ ግብር ወጥቶላቸው የነበረ ቢሆንም የቀን ሽግሽግ መደረጉን ካፍ አስታውቋል፡፡

በዚህ መሰረትም ከማላዊ ጋር የሚደረገው ጨዋታ ግንቦት 28 ቀን የሚከናወን ሲሆን፥ ከግብጽ ጋር የሚከናወነው ጨዋታ ደግሞ ሰኔ 2 ቀን 2014 የሚደረግ መሆኑን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.