Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ የወጣቶች በጎ ፈቃድ ማህበራዊ አገልግሎት የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 17 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከታህሳስ 5 አስከ 16 ቀን 2013 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው ብሔራዊ የወጣቶች በጎ ፈቃድ ማህበራዊ አገልግሎት የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል፡፡
መድረኩ በኢትዮጵያዊ በጎ እሴቶች የተገነቡ መልካም ግንኙነቶች የተንፀባረቁበት እና መግባባቶች የተፈጠሩበት እንደሆነ ተሳታፊዎች ገልፀዋል፡፡
ወጣቶቹ በነበራቸው ቆይታ በበጎ አመለካከት፣ መልካም ሥነ-ምግባር፣ አብሮነት፣ ዓለም ዓቀፍ ተወዳዳሪነት፣ ስራ ፈጣሪነት፣ ውጤታማነት፣ ዓላማ ያለውን ሕይወት የመምራት ክሕሎት፣ ማህበረሰባዊ ተግባቦት፣ እንዲሁም በራስ የመተማመን ብቃት ላይ ግንዛቤ የሚፈጥሩ ሰነዶች ቀርበው በጥልቀት ሲወያዩ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡
በስልጠናው ኢትዮጵያ የተረጋጋች፣ ሰላም የሰፈነባት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት የተረጋገጠባት ሀገር እንድትሆን ወጣቶች የላቀ ድርሻ እንዳላቸው ግንዛቤ አግኝተው ለሀገር ግንባታው የየበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ የሚረዳቸው ንቅናቄ የተፈጠረበት የስልጠና መድረክ እንደሆነም ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
አያይዘውም በምንሰማራበት የበጎ ፈቃድ ማህበራዊ አገልግሎቶቻችን የወንድማማችነት ትስስር የምናጠናክርበት፤ የሀገርና የዜግነት ክብር እና ፍቅር የምንገነባበት እንደሚሆን እምነታችን ነው ሲሉ አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል፡፡
ከዚያም ባለፈ የተለየ ውብ ቀለም ያላቸው ኢትዮጵያዊ በጎ እሴቶቻችንን ያወቅንበት፣ የተለዋወጥንበት እናም ለበጎ አድራጎት ተግባር ለመጠቀም እንድንዘጋጅባቸው ትልቅ መነሳሳትን ብሎም መነቃቃትን ነው ማለታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.