Fana: At a Speed of Life!

ብሪታኒያ በ2ኛው ዙር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ውስጥ መሆኗ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 23 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአውሮፓ እያገረሸ ያለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ብሪታኒያን ስጋት ውስጥ እንደከተታት የሀገሪቱ ጤና ሚኒስትር ማት ሀን ኮክ  ገለጹ።

ይህንን ስርጭት ለመቆጣጠርም ዳግም ከሌሎች ሀገራት የሚመጡ ዜጎች ላይ አስገዳጅ  የማቆያ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል ብለዋል ።

በአውሮፓ ያገረሸው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሀገሪቱ እንዳትጎዳ አዳዲስ እርምጃዎችንም ልንወስድ እንችላለን ብለዋል ሚኒስትሩ ።

ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በተለይ ከስፔን የሚመጡ መንገደኞች ለ14 ቀናት አስገዳጅ ማቆያ እንዲገቡ መደረጉ ይታወሳል ።

ዳግም ባገረሸው የኮኖና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ስዊድንም  ከጎረቤቶቿ ጋር ይደረግ የነበረ ጉዞን አቋርጣለች ።

ምንጭ፡-ሮይተርስ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.