Fana: At a Speed of Life!

ብርሃኑ ለገሰ የቶክዮ ማራቶንን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በጃፓን ቶክዮ በተካሄደው የማራቶን ውድደር ኢትዮጵያዊው ብርሃኑ ለገሰ አሸናፊ ሆነ።
 
ብርሃኑ ውድድሩን 2 ሰዓት ከአራት ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመጨረስ ነው አንደኛ ሆኖ ያጠናቀቀው።
 
በማራቶን ሩጫው 38 ሺህ ሰዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ቀድሞ እቅድ ቢያዝም በኮሮናቫይረስ ምክንያት 200 ሰዎች ብቻ ውድድሩ ላይ እንዲሳተፉ ተደርጓል።
 
የቶክዮ ማራቶን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያትም ደብዝዟል።
 
ጃፓን በዚህ ቫይረስ ምክንያት ሰዎችን የሚያሰባስቡ ስፖርታዊ ውድድሮች እስከ ፈረንጆቹ መጋቢት አጋማሽ ድረስ እንዳይካሄዱ አግዳለች።
 
ዘንድሮ የዓለም ኦሎምፒክን የምታስተናግደው ሀገሪቱ፥ ይህ ውድድር ግን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደሚካሄድ ነው ያስታወቀችው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.