Fana: At a Speed of Life!

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በተለያዩ ቋንቋዎች የተተረጎመውን ቃለ ዐዋዲ በይፋ መረቁ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በተለያዩ ቋንቋዎች የተተረጎመውን ቃለ ዐዋዲ በይፋ መረቁ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምትመራበት ቃለ ዐዋዲ በሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ አማካኝነት በእንግሊዘኛ ፣ኦሮምኛና ትግርኛ ቋንቋዎች የተተረጎመ ነው፡፡
ቃለ ዐዋዲውንም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በይፋ መመረቃቸውን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በምረቃ ስነስርዓቱም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ያሬድ፣ የሰበካ ጉባዔ ማደራጃና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያው ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.