Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ በምርጫ ነክ ወንጀሎች ዙሪያ ለመርማሪ ፖሊሶችና ዐቃቢያን ሕጎች ሥልጠና ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ነክ ወንጀሎች ዙሪያ ለመርማሪ ፖሊሶችና ዐቃቢያን ሕጎች ሥልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  በምርጫ ነክ ወንጀሎች ዙሪያ ለመርማሪ ፖሊሶች እና በምርጫ ነክ ክስ አቀራረብ ዙሪያ ለዐቃቢያን ሕግ   ሥልጠና  ሰጥቷል።

በወቅቱም የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ውብሸት አየለ ባደረጉት ንግግር ÷ሥልጠናው የሀገሪቱን የምርጫ  ሕግ ለማወቅ የሚያስችል  መሆኑን ተናግረዋል።

ምርጫ ሰላም ባለበት ቦታ መካሄድ እንዳለበት በመግለጽ ለዚህም የሰላም አስከባሪዎችና የፍትሕ አካላት ሚና ላቅ ያለ መሆኑን  ገልጸዋል።

የቦርዱ የሕግ ክፍል ቡድን መሪ የሆኑት ወንጌል አባተ በበኩላቸው ÷ ሥልጥናው የምርጫ ነክ ወንጀሎች ላይ ምርመራ እንዲሁም ክሥ የሚያቀርቡ ፖሊሶችንና ዐቃቢያን ሕግን ዐቅም ማሳደግና መደግፍ ዐላማ  ማድረጉን ገልጸዋል።

ይህም ምርጫው ነፃ፣ ሰላማዊ እና ተዓማኒ ሆኖ ይከናወን ዘንድ በምርጫው ላይ ቁልፍ ባለድርሻ አካላትን ማሣተፍ ተገቢ በመሆኑ÷ አጠቃላይ የኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ አጭር ዳሰሳ እንዲሁም የወንጀል ድንጋጌ እና የሥነ-ምግባር ጥሰቶችን በተመለከተ ከዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና ከአጠቃላይ የወንጀል ሕጉ አንጻር ሥልጠና እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

ሠልጣኞቹ በምርመራ እና ክሥ አቀራረብ ላይ የሚኖራቸውን ዝርዝር ሚና እና ኃላፊነት እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በሚወጡበት ሂደት ሊከተሉት የሚገባውን የአሠራር ሥርዓትና ተፈጻሚነት ያላቸው ሕጎች በዝርዝር በሚዳስስ ሁኔታ መሰልጠናቸውን ከብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.