Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ በ673 የምርጫ ክልሎች የምርጫ ቁሳቁስ መጓጓዙን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ673 የምርጫ ክልሎች የምርጫ ቁሳቁስ መጓጓዙን አስታወቀ።

በየደረጃው የሚገኙ የክልል አመራሮች ለምርጫ ቁሳቁስ ማጓጓዣ እንዲተባበሩ ጠይቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመራጮች የምዝገባ መረጃና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር እየተወያየ ነው።

በውይይቱ ቦርዱ በመራጮች መረጃ፣ በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂና በምርጫ ቁሳቁስ ማዳረስ እስካሁን ያከናወናቸውን ሥራዎች አብራርቷል።

በእስካሁን ሂደት በ673 የምርጫ ክልሎች የምርጫ ቁሳቁስ መጓጓዙን አስታውቋል።

በ50 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ እየተጓጓዘ መሆኑን የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ መግለጻቸውን ከኢዜአ ዘግቧል።

ሰብሳቢዋ የምርጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች ለማድረስ የማጓጓዣ ችግር መኖሩን ጠቅሰው በየደረጃው የሚገኙ የክልል አመራሮች ለችግሩ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.