Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ እጩ ተወዳዳሪዎች የምዝገባ ድጋፍ ፊርማ አሰባሰብና የመለያ ምልክት አመራረጥ መመሪያ ቁጥር 7/2013 አንቀጽ 16 (2) እንዲሰረዝ ወሰነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ  እጩ ተወዳዳሪዎች የምዝገባ ድጋፍ ፊርማ አሰባሰብና የመለያ ምልክት አመራረጥ መመሪያ ቁጥር 7/2013 አንቀጽ 16 (2) እንዲሰረዝ ወሰነ፡፡

ይህ የሆነው የተፈጠረውን መምታታት ለመፍታት መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ይህንን ተከትሎም ማንኛውም እጩ ለመመዝገብ ያለ ደመወዝ ፍቃድ የማያስፈልገው መሆኑን አጽንኦት በመስጠት የዚህን የአሰራር ክፍተት ለመድፈን ለምርጫ ክልል ጽህፈት ቤት አስፈጻሚዎች ይኸው መልእክት እንዲተላለፍ የሚደረግ መሆኑን ቦርዱ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የእጩዎች ምዝገባን እያከናወነ እንደሆነ ተገልፆ ቦርዱ የእጩዎች ምዝገባ ሂደቱን በመገምገም እንዲሁም ከፓለቲካ ፓርቲዎች የሚቀርቡ አቤቱታዎችን በማገናዘብ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታትም እየሰራ ነው ተብሏል።

በመሆኑም በአዋጅ 1162/2011 እንዲሁም በእጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ ድጋፍ ፊርማ አሰባሰብና የመለያ ምልክት አመራረጥ መመሪያ ቁጥር 7/2013 አንቀጽ 16(1) መሰረት የመንግስት ሰራተኛ እጩዎች ስራቸውን መልቀቅ ሳያስፈልጋቸው በእጩነት ለመወዳደር እንደሚችሉ ይደነግጋል።

እንዲሁም እጩ ከሆኑ በኃላ በምርጫ ወቅት ያለደምወዝ ፈቃድ የማግኘት መብታቸውም በህግ የተሰጠ ነው።

ቦርዱ የእጩዎች ምዝገባን በሚያከናውንበት ወቅት በእጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ ድጋፍ ፊርማ አሰባሰብና የመለያ ምልክት አመራረጥ መመሪያ ቁጥር 7/2013 አንቀጽ 16(2) ትርጉም ተዛብቶ በመወሰዱ የተለያዩ የምርጫ ክልሎች የመንግስት ሰራተኛ እጩዎችን ያለደምወዝ ፈቃድ የተወሰደበትን ሰነድ እንዲያቀርቡ መጠየቃቸውን ተረድቷል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የተፈጠረውን መምታታት ለመፍታት እጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ ድጋፍ ፊርማ አሰባሰብና የመለያ ምልክት አመራረጥ መመሪያ ቁጥር 7/2013 አንቀጽ 16 (2) እንዲሰረዝ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.