Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አካሄደ።

የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በተገኙበት በዚህ ውይይት የፓለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፈዋል።

በውይይቱ የምርጫ ሂደቱ የእስካሁን ጉዞና በሂደቱ ያጋጠሙ ሁኔታዎች ትኩረት ተደርጎባቸዋል።

በዋናነትም ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ ሂደት ጋር በተገናኘ ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ እና ያጋጠሙ ችግሮችን አቅርቧል።

ለምዝገባው አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶች ማጓጓዝ ጋር በተገናኘ የገጠሙ ችግሮችን ለመፍታት ቦርዱ የሰራቸውን ስራዎችንም አቅርቧል።

በ674 የምርጫ ክልሎችና 50 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች ቁሳቁሶቹን ለማሰራጨት መሰራቱ ተገልጿል።

የቦርድ ሰብሳቢዋ ከትራንስፓርት ችግር በተጨማሪ ሌሎች እንቅፋት የነበሩ ተግዳሮቶችን ጠቅሰዋል።

በዚህም የልዩ ምርጫ ጣቢያዎች (ማለትም ተፈናቃዬች የሚገኙባቸውና ወታደራዊ መኖሪያዎች አካባቢ) ማደራጀት መዘግየት፣ በየተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የጸጥታ ችግሮች፣ የተጣበበ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ዋና ዋና ችግሮች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ በጸጥታ ችግር ምክንያት የመራጮች ምዝገባ የዘገየባቸው እና ያልተጀመረባቸው አካባቢዎችንም ይፋ አድርገዋል።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.