Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ባወጣው መመሪያ ላይ የሕዝብ አስተያየት ለመቀበል ጥሪ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀጣይ በሚደረገው 6ኛ ሃገራዊ የምርጫ ሂደት ወቅት የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ባወጣው መመሪያ ላይ የሕዝብ አስተያየት ለመቀበል ጥሪ አድርጓል።

የመመሪያው ዋና ዓላማ በምርጫ ሂደት ወቅት የኮቪድ19 ስርጭትን መከላከል እና መቆጣጠር በቅድመ ምርጫ፣ በድምፅ መስጫ ቀን እና በድኅረ ምርጫ ወቅት ከምርጫ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ተግባራት ሁሉ የኮቪድ-19 ስርጭትን እንዳይጨምሩ ማድረግ መሆኑንም ገልጿል።

ለቦርዱ እና ለምርጫ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ለምርጫ አስፈጻሚ አካላት በሙሉ ሊሟሉላቸው የሚገቡ ሁሉም የኮቪድ-19 አስፈላጊ መስፈርቶች የረቂቅ መመሪያው የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውንም አስታውቋል።

በመሆኑም ረቂቅ መመሪያው ላይ አስተያየት ያላቸው አካላት ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በlegal@nebe.org የኢ-ሜይል አድራሻ እንዲሁም በድረ ገጹ መልዕክት ማስቀመጫ አማካኝነት ለቦርዱ የሕግ ክፍል መላክ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳ
የፋና ድረ ቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.