Fana: At a Speed of Life!

ቦይንግ ካምፓኒ ለተጎጂዎች ለመክፈል ቃል የገባውን የ500 ሚሊየን ዶላር ካሳ መክፈል ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  የቦይንግ ካምፓኒ ምርት የሆኑ ሁለት አውሮፕላኖች እኤአ በ2018 በኢንዶነዢያ እንዲሁም በ 2019 ደግሞ በኢትዮጵያ አደጋ ለገጠማቸው ተጎጂ ቤተሰቦች ለመክፈል ቃል የገባውን የ500 ሚሊየን ዶላር የካሳ ክፍያ መስጠት መጀመሩ ተገለጸ፡፡

በሁለቱ በረራዎች ወቅት በደረሰ የመከስከስ አደጋ የ346 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡

እኤአ በ2019 መነሻውን አዲስ አበባ በማድረግ ወደ ኬኒያ ሲበር በነበረው አውሮፕላን ላይ በደረሰው የመከስከስ አደጋ የ149 ሰዎች ህይወት ማለፉና ከነዚህ ውስጥም 32 ኬንያውያን እንደነበሩ ይታወቃል፡፡

የኬንያውያኑ ተጎጂ ቤተሰቦች በካምፓኒው ላይ መስርተውት የነበረውን ክስ ለማንሳት ፈቃደኛ በመሆናቸው የካሳ ክፍያው ባለፈው ሀሙስና አርብ ወደ እያንዳንዳቸው የባንክ አካውንት ገቢ እንደተደረገላቸው ተዘግቧል፡፡

ይህን የገለጹት ከ90 በላይ የአደጋው ተጎጂዎችን ጉዳይ በመያዝ በፍርድ ቤት ሲከራከር የነበረው የሪቤክ የህግ ቻርተርድ ሀላፊ ማኑኤል ቮን መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አደጋዎቹ ከተከሰቱ በኋላ የቦይንግ ካምፓኒ ከኤር ባስ ጋር ተወዳድሮ ትርፋማ እንዳይሆን ተጽዕኖ ውስጥ ወድቆ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.