Fana: At a Speed of Life!

ተመራማሪዎች በህዋ ላይ ከፍተኛ ፍንዳታ መከሰቱን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠፈር ተመራማሪወች በህዋ ላይ የከፍተኛ ፍንዳታ ክስተት መመልከታቸውን አስታወቁ።

ለይተነዋል ያሉት ፍንዳታ እስካሁን ከታዩት ከፍተኛውና በርካታ የከዋክብት ስብስብን በያዘው ረጨት (ጋላክሲ) ላይ ትልቅ ሽንቁር ፈጥሯልም ነው ያሉት።

ፍንዳታው ከምድር 390 ሚሊየን የብርሃን አመታት ርቀት ላይ ከሚገኘው የበርባኖስ (ጥልቁ ጨለማ) ክፍል ሳይነሳ እንዳልቀረም ገልጸዋል።

በቴሌስኮፕ በታገዘ ባደረጉት ምልከታም በፍንዳታው ከበርባኖሱ የሚመነጨው ሃይል የከዋክብት ስብስቡን ወደራሱ ማጠፍ ስለመቻሉም ጠቅሰዋል።

የፍንዳታውን ሂደት ለመመልከት የአውስትራሊያ እና የህንድ ቴሌስኮፕን ተጠቅመዋል።

ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ ያሉ አጠቃላይ ዝርዝር መረጃዎችን በተመለከተ ግን ያሉት ነገር የለም።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.