Fana: At a Speed of Life!

ተመራማሪዎች አይቡፕሮፊን የተባለውን ማስታገሻ ለኮሮና ቫይረስ ህክምና እንዲውል ሙከራ እያደረጉበት ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ተመራማሪዎች አይቡፕሮፊን የተባለውን ማስታገሻ መድሃኒት ለኮሮና ቫይረስ ህክምና እንዲውል ሙከራ እያደረጉበት ነው።

ከሁለት ኮሌጆች የተውጣጣው የተመራማሪዎች ቡድን መድሃኒቱን በሆስፒታል ውስጥ የሚገኙ የኮሮና ቫይረስ ህሙማንን ይታደጋል በሚል ሙከራውን እያደረገ ነው።

የቡድኑ አባላት መድሃኒቱ በመሳሪያ አጋዥነት (ቬንትሌተር) የሚተነፍሱ ህሙማንን ያግዛል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

በሙከራው ለህሙማኑ ከሚደረገው ክትትል እና ከሚሰጠው ህክምና በተጨማሪነት አይቡፕሮፊን የተባለው ህመም ማስታገሻ መድሃኒት ይሰጣቸዋል ነው የተባለው።

በሚደረገው ሙከራ አሁን ገበያ ላይ ያለው ሳይሆን በተለየ ሁኔታ የተቀመመው መድሃኒት ጥቅም ላይ እንደሚውል ተገልጿል።

ሙከራ የሚደረግበት የአይቡፕሮፊን አይነት የመገጣጠሚያ አካባቢ ህመም ያለባቸው ሰዎች ለማስታገሻነት የሚጠቀሙበት ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.