Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሀሪስ ቃለ መሀላ ፈፀሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ዴሞክራቱ ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በመሆን ዛሬ በነጩ ቤተመንግስት ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከፍተኛ የፖለቲካ መከፋፈል፣ የኢኮኖሚ ቀውስ እና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን በሀገሪቱ ላይ ከፍ ያለ ጉዳት እያስከተለ በሚገኝበት ወቅት ላይ በዓለ ሲመታቸው ተካሂዷል

በዛሬው ዕለት የመጀመሪያዋ ጥቁር እስያዊት ሴት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን የተመረጡት ካማላ ሃሪስም ቃለ መሃላ ፈፅመው ወደ ነጩ ቤተመንግስት ገብተዋል።

በዋሽንግተን የሚገኘው የካፒቶል ሂል በዶናልድ ትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች ጥቃት ከተፈፀመበት በኋላ ዋና በ50ዎቹ ግዛቶች ከፍተኛ የፀጥታ ቁጥጥር እየተካሄደ ይገኛል።

ለጆ ባይደን በዓለ ሲመት ብቻም 25 ሺህ ወታደሮች የፀጥታ ቁጥጥር ለማድረግ በዋሽንግተን ተሰማርተዋል።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ምክንያት የጆ ባይደን በዓለ ሲመት ስነ ስርዓት እንደተለመደው በርካታ ህዝብ ሳይገኝ ነው የተካሄደው።

በዚህ በዓለ ሲመት ላይ የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንቶች ባራክ ሁሴን ኦባማ ፣ ቢል ኪሊንተን እና ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ተገኝተዋል።

ተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዚህ በዓለ ሲመት ሳይገኙ ወደ ፍሎሪዳ አቅንተዋል።

በሌላ በኩል ተሰናባቹ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ግን በስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.