Fana: At a Speed of Life!

ተመድ በሰሜን ምስራቅ ናይጀሪያ የሚያደርገውን የሰብዓዊ ድጋፍ በጊዜያዊነት አቋረጠ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 11 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ በናይጄሪያ ሰሜን ምስራቅ ቦርኖ ግዛት በዲካ እና በዳማክ ከተሞች የሚያደርገውን ሰብአዊ ድጋፍ በጊዜያዊነት ማቋረጡን አስታወቀ፡፡

ተመድ ድጋፉን ያቋረጠው ቦኮ ሃራም በአካባቢው ከሚፈጽመው ጥቃት ጋር ተያይዞ መሆኑ ታውቋል፡፡

በናይጄሪያ የተመድ የሰብአዊ ድጋፍ አስተባባሪ ኤድዋርድ ካሎን፥ የሰብአዊ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅና ወደ ሌላ ቦታ ለማዛወር በተጠቀሱት አካባቢዎች ለጊዜው ስራ አቁመናል ብለዋል።

አስተባባሪው አያይዘውም ሁኔታውንም በቅርብ እየተከታተልን ነው÷ ድርጅቱ በተቻለ መጠን ድጋፉን መቀጠል እንደሚፈልግና የተጎዱ ዜጎችም ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ገልጸዋል፡፡

ከሳምንት በፊት በተፈጸመ ጥቃት አራት ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ ሰብአዊ ድጋፍ መስጫ ጣቢያዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

ጥቃቱ ወደ 8 ሺህ 800 ሰዎችን ሲያፈናቅል 76 ሺህ ሰዎችን ደግሞ በሚደረግላቸው የሰብአዊ ድጋፍ እና ጥበቃ  ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ብሏል ፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.