Fana: At a Speed of Life!

ተመድ የህብረቱ ሊቀ መንበር በህዳሴው ግድብ ላይ ሶስቱን ሃገራት ወደ ስምምነት ለማምጣት ለሚያደርጉት ጥረት ሙሉ ድጋፍ እንዳለው አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሲሪል ራማፎሳ በህዳሴው ግድብ ላይ ሶስቱን ሃገራት ወደ ስምምነት ለማምጣት ለሚያደርጉት ጥረት ሙሉ ድጋፍ እንዳለው አስታወቀ፡፡

የድርጅቱ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የህብረቱ ሊቀ መንበር ራማፎሳ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንን እና ግብጽን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ወደ ስምምነት እንደሚጡ እያደረጉት ላለው ጥረት ሙሉ ድጋፍ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

በድርድሩ ሂደትም ተመድ ሙሉ ድጋፍ ያደርጋል ማለታቸውን በተመድ ከኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ የትዊተር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ድርድሩ በወንድማማችነት መንፈስ፣ በጋራ ተጠቃሚነት እና በስምምነት ይቋጭ ዘንድ የተፋሰሱ ሃገራት ጠንካራ ስራ ሊሰሩ ይገባል ማለታቸውን የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪች ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም ታላቁ የህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ መካከል ትልቅ የትብብር እና የአጋርነት መሳሪያ መሆን እንደሚችልም አንስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.