Fana: At a Speed of Life!

ተመድ 3 ሚሊየን ሶማሊያውያንን ለመደገፍ 1 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የረድኤት ድርጅቶች 3 ሚሊየን ሶማሊያውያንን ለመደገፍ 1 ቢሊየን 30 ሚሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ ገለጹ።

ተመድ እና ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅቶች የ2020 የሶማሊያ ሰብዓዊ ድጋፍ ምላሽ እቅድን ይፋ አድርገዋል።

በእቅዳቸው መሰረትም ለሶማሊያውያን ድጋፉን ለማድረስ ገንዘቡ እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል።

ድጋፉ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችን ለማድረስ፣ ለጤና፣ ትምህርት፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ ለደህንነት ስጋት ቅነሳ እና ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሚውል ነው ተብሏል።

ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሶማሊያውያን ከድህነት ወለል በታች እንደሚገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ።

በዚህ ሳቢያም አብዛኛዎቹ ለምግብ እና ለአልሚ ምግብ እጥረት የተጋለጡ ናቸው።

ምንጭ፡- ሲ ጂ ቲ ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.