Fana: At a Speed of Life!

ተሳፋሪዎች ርቀታቸውን እንዲጠብቁ በማድረግ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን መከላከል እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)ተሳፋሪዎች ርቀታቸውን እንዲጠብቁ በማድረግ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን መከላከል እንደሚገባ ተገለፀ።

የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት አ.ማ የተሠራውን ሥራ ጎብኝተዋል።

በዚህ ወቅት እንደገለፁት ተሳፋሪዎች ትኬት ሲቆረጡ፣ ሲሳፍሩም ሆነ በመቀመጫቸው ተገቢውን ርቀት በመጠበቅ የተሳፋሪዎች ጥግግት እንዲቀንስ ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት አ.ማ አሁን አገልግሎት እየሰጠ ባለው ከአዲስ አበባ-ድሬዳዋ መስመር የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ባቡሮችን በመነሻ እና በመዳረሻ ቦታዎች በኬሚካል እንዲፀዱ የማድረግ፤ ተሳፋሪዎች ወደ ባቡሩ በሚገቡበት ወቅት የሙቀት መጠናቸውን የመለካት ሥራ መሰራቱን፣ እጃቸውን በውሀ፣ በሳሙና እንዲሁም በአልኮልና ሳኒታይዘር እንዲታጠቡ የማድረግ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.