Fana: At a Speed of Life!

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ ለኢድ ዓል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ ለ1ሺህ 442ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ ዓል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
በመልዕክታቸው በዓሉን 13 ተግባራትን በመከወን ማክበር እንደሚገባ ጠቅሰው ከእነዚህ ውስጥ የኢድ ሰላት ከመሄዳችን በፊት ሰደቀተን ፊጥር ማውጣት እንደሚገባና በተለይም ደግሞ በዓሉን ከአቅመ ደካሞች ጋር ማክበር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የኢድ ሰላትን ስናደርግም በሰላምና በተክቢር ሰግደን መመለስ ይገባልም ነው ያሉት፡፡
በተለይም አሁን በሃገሪቱ እየተፈጠሩ ያሉ መልካም ያልሆኑ ነገሮችን አላህ እንዲያነሳልን ፀሎት ማድረግ አለብን ብለዋል፡፡
በሌላ በኩልም በዓሉን እራስን ከኮሮና ቫይረስ በመጠበቅ ማክበር እንደሚገባ ጠቅሰው፥ የወጡ መመሪያዎችን መተግበር አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የኢድ ዓል ፈጥር በዓል ዛሬ ማታ ጨረቃ ከታየች ነገ ካልታየች ደግሞ ሃሙስ እንደሚከበር ገልፀዋል፡፡
በዓሉ እንደከዚህ ቀደሞቹ ዘንድሮም በአደባባይ እንደሚከበር ተናግረዋል፡፡
በፈትያ አብደላ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.