Fana: At a Speed of Life!

ተቋሙ የሱሉልታ – ደብረ ማርቆስ ባለ 400 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊ መስመር ተሸካሚ ምሰሶ እየጠገንኩ ነው አለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓባይ ሸለቆ ውስጥ በመሬት መንሸራተት ጉዳት የደረሰበት ከሱሉልታ – ደብረ ማርቆስ የተዘረጋው ባለ 400 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊ መስመር ተሸካሚ ምሰሶ የጥገና ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
ከመጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ያለው የከፍተኛ ቮልቴጅ መስመር ጥገና÷ ለሰባት ቀናት ኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ የሚከናወን ቢሆንም በርካታ አካባቢዎች ኃይል እንዳያጡ ለማድረግ ግሪዱ ለሁለት ተከፍሎ አገልግሎት እንዲሰጥ እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡
በጥገና ሥራው የተነሳ በግሪዱ ላይ የደረሰው ጫና ከ 4 በመቶ ያልበለጠ ሲሆን÷ ይህም የግሪድ ሲስተሙ የተረጋጋ እንዲሆንና ያልተቆራረጠ ኃይል ለህብረተሰቡ ለማቅረብ እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡
ይሁንና ግሪዱ ለሁለት ተከፍሎ በመስራቱ የተፈጠረው ጫና አነስተኛ ቢሆንም÷ በአንዳንድ አካባቢዎች ከስርጭት መስመሮች መቋረጥ ጋር ተያይዞ የሲስተም አለመረጋጋትና በአንዳንድ አካባቢዎች የኃይል መቆራረጥ መኖሩን የገለጸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል÷ የጥገና ሥራው እስከሚጠናቀቅ የሚኖረውን የኃይል መቋረጥ የቆይታ ጊዜ ለመቀነስ ሰፊ ሥራዎች እየሰሩ ነው ብሏል፡፡
ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞች ይህንን በመገንዘብ የተጀመረው የጥገና ስራ እስከሚጠናቅቅ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ መጠየቁን ከኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.