Fana: At a Speed of Life!

ተቋርጦ የነበረው ንብረትን በስጦታ የማስተላለፍ ውል ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከብር ኖት ቅየራው ጋር ተያይዞ ተቋርጦ የነበረው ንብረትን በስጦታ የማስተላለፍ ውል ከዛሬ ጀምሮ መሰጠት መጀመሩን የፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን አማረ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ከመስረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሲሸጥ ክፍያ የተፈጸመበት የባንክ ደረሰኝ ይጠየቅ የነበረውን ተቋሙ እንደአሰራር ይዞት የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።

ከ51 በላይ አገልግሎቶችን እየሰጠ የሚገኘው ኤጀንሲው 70 በመቶ የሚሆነውን አገልግሎት በኦንላይን እንደሚሰጥ አስታውቋል።

ከቀጣዩ ጥር 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ አገልግሎት እንደሚጀምር ያስታወቁት ዋና ዳይሬክተሩ   ተቋሙ የአክሲዮን እና ሃላፊነታቸው የተወሰነ የግል ማህበራት መመስረቻቸውን፣ መተዳደሪያና ቃለጉባኤያቸውን በመላክ ጉዳያቸውን በኦንላይን የሚጨርሱበት ስርዓት እንደሚጀምሩ ገልጸዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ እንደገለጹት ከሆነ አዲሱ አሰራር በስራ ላይ ሲውል አክሲዮን ማህበራቱ ለመፈረም ብቻ ወደ ተቋሙ እንደሚመጡም አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ አገልግሎቱን መስጠት የጀመረው ኤጀንሲው በአብዛኛው የቤተሰብ፣ የጠቅላላ እና የጠበቃ ውክልና የአገልግሎቱን 50 በመቶ ያህል እንደሚሸፍን ነው የተጠቀሰው፡፡

እንዲሁም ንብረትን በስጦታ ወይም በሽያጭ ለማስተላለፍ 20 በመቶ የሚሆነውን ተገልጋይ ያስተናግዳል ተብሏል፡፡

ኤጀንሲው በየዕለቱ ከ12 ሺህ በላይ ተገልጋዮችን እንደሚያስተናግድም ተገልጿል፡፡

 

በፈቲያ አብደላ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.