Fana: At a Speed of Life!

ተቋርጦ የነበረው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ህብረት የሚመራውና ለጊዜው ተቋርጦ የነበረው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ እንደሚቀጥል የውሃ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ እንደገለፀውም በአፍሪካ ህብረት መሪነት ለ11 ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ከሁለት ሳምንታት በፊት የተቋረጠው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ከሳምንት በፊት ሊቀጥል የነበረ ቢሆንም በሱዳን በኩል በቀረበው ለአንድ ሳምንት የይዘግይልኝ ጥያቄ መሠረት ለአንድ ሳምንት ዘግይቷል፡፡

በመሆኑም ተቋርጦ የነበረው ድርድር ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ለቀጣይ አንድ ሳምንት እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

የዚህ ሳምንት ድርድር ቀደም ሲል ከተካሄደው የ11 ቀናቱ ድርድር በኋላ ለመሪዎች በቀረበው ሰነድ መሠረት መሪዎቹ ባስቀመጠጡት አቅጣጫ የሚቀጥል እንደሆነም ታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ኢትዮጵያ እንደ ከዚህ ቀደሙ ፍትሃዊና ምክንያታዊ ተጠቃሚነትን መሠረት ባደረገ ሁኔታ ሁሉንም ወገን ተጠቃሚ ባደረገ መልኩ ድርድሩን ለመቋጨት ትሠራለች ብሏል።

 

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዘናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.